በትራንስፖርት ቢሮ 9417 በነፃ የስልክ ጥሪ እ......

ዝርዝር ዜና

አቃቂ ቃሊቲ ትራንስፖርት ቅ/ፅ/ቤት

በትራንስፖርት ቢሮ 9417 በነፃ የስልክ ጥሪ እየቀረቡ ያሉ የህዝብ ቅሬታዎች ምላሽ እየተሰጠባቸው መሆኑ ተገለፀ

ግንቦት 23-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

በትራንስፖርት ቢሮ 9417 በነፃ የስልክ ጥሪ እየቀረቡ ያሉ የህዝብ ቅሬታዎች ምላሽ እየተሰጠባቸው መሆኑ ተገለፀ፡፡ በአዲስ አበባ የትራንስፖት ቢሮ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ህብረተሰቡ በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቢሮው ነፃ የስልክ ጥሪ መስመር 9417 ጥቆማዋችን በመቀበል ለህዝብ ቅሬታዎች ምላሽ እየሰጠ ይገኛል፡፡ በቢሮው የነፃ የስልክ ጥሪ ማዕከል ባለሙያዎች ህብረተሰቡ በየቀኑ በነፃ መስመሩ እየሰጠ ያለው ጥቆማና አስተያየት እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡ በነጻ የስልክ መስመሩ በድግግሞሽ የሚቀርቡ ቅሬታዎቹም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች መስመር ማቆራረጥ፣ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ መሳደብ እና ከተፈቀደው የመጫን አቅም በላይ በመጫን ተሳፋሪ ማጉላላት ሲሆኑ ሌሎችም ከተጠሪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥና መረጃ ለመጠየቅ ወደ ጥሪ ማዕከሉ እንደሚደወል አስታውቀዋል፡፡ እነዚህን ጥቆማዎች መነሻ በማድረግም፤ ጥቆማው ወደ ተሰጠበት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት መረጃውን በመላክ ቅሬታው የሚፈታ ሲሆን፤ ህብረተሰቡም ከህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ጋር ተያይዞ ለሚኖረው አስተያየትና ጥቆማ ወደ ማዕከሉ ስልክ ሲደውሉ ጥፋት ያጠፋውን ተሽከርካሪ ሰሌዳ፣ የጉዞውን መነሻና መድረሻ እንዲሁም ሰዓቱን ጭምር መረጃ በመያዝ እንዲያቀርብ ተጠቁሟል፡፡ ህብረተሰቡም ከትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ጋር ተያይይዞ ለሚሰጣቸው ጥቆማዎችና አስተያየቶች በቢሮው ነጻ የስልክ መስመር 9417 ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከጠዋት 2፡00 አስከ ምሽት 2፡00 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ቢሮው ያሳውቃል፡፡